14ኛው በአማራ ክልል የሚገኙ የፌዴራል መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የጋራ  የውይይት ጉባዔ ተካሂደ፡፡

DSC_0501

14ኛው በአማራ ክልል የሚገኙ የፌዴራል መንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የውይይ ጉባዔ በደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የመሰብሰቢያ አዳራሽ ከጥር 19-20/2009 ዓ.ም የክልል ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት በድምቀት ተከናውኗል፡፡ ጉባዔውን በንግግር የከፈቱት የደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ኘሬዚዳንት ዶ/ር አለማየሁ ከበደ በጋራ አስበንና ተመካክረን ላቋቋምነው ለ14ኛው የጋራ የምክክር መድረክ ለመሳተፍ ወደ ደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ  ለመጡ ተሳታፊዎች እንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡     ኘሬዚዳንቱ የደብረ […]

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ለተመራቂ ተማሪዎች የኢንተርፕረነርሽፕ ስልጠና መስጠቱን አስታወቀ፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት ክፍሎች ሲያሰለጥናቸው የቆዩ ከ600 በላይ ተመራቂ ተማሪዎችን ከኢትዮጵያ ኢንተርፕርነርሽፕ ማእከል ጋር በመተባበር ለ4 ቀናት ያህል በስራ እድል ፈጠራ ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና እየሰጠ ነው፡፡የስልጠናው አስተባባሪ  በዩኒቨርሲቲው የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ ፋኩልቲ ም/ዲን አቶ ግዛቸው ጥላሁን ፤የስልጠናው ዋና አላማ ተማሪዎቹ ከምርቃን በኋላ በተለያዩ የስራ መስኮች ለመሰማራት የሚያስችል ግንዛቤ እንዲኖራቸው  ነው ብለዋል፡፡ ስልጠናውን የሰጡት የኢትዩጵያ ኢንተርፕርነርሽፕ […]

የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ የቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት ትምህርት ክፍል ቱሪዝምን ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከአጋር አካላት ጋር ውይይት አካሄደ፡፡

የትምህርት ክፍሉ በደብረታቦር ከተማ ለሚገኙ የሆቴል ባለሀብቶች እና ስራ አስኪያጆች በሆስፒታሊቲ ኢንዱስትሪ ምንነት ዙሪያ ስልጠና በመስጠት ላይ ነው፡፡ የትምህርት ክፍል ኃላፊው አቶ እርጥባን ደመወዝ የደብረታቦር ከተማ ጥንታዊና እምቅ የቱሪዝም ሀብት ያለበት አካባቢ በመሆኑ ጠንክረን በመስራት ዘርፉን ማሳደግ አለብን ብለዋል፡፡ የመወያያ ፅሑፉን  ያቀረቡት የቱሪዝም ማኔጅመንት መምህር አቶ ፍርድ ይወቅ አበበ ቱሪዝምን ለማሳደግ የሆስፒታሊቲን ፅንሰ ሀሳብ ማወቅ […]

የግንቦት ሃያ የድል ውጤቶችን በማጠናከር የተጀመረውን ልማት ማስቀጠል እንደሚገባ የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ማህበረሰብ አባላት ተናገሩ ፡፡

የማሽቆልቆል ምዕራፍ ተዘግቶ የእድገት ምዕራፍ የተከፈተበት የሩብ ምዕት አመት የትግልና የድል ጉዞ በሚል ርዕስ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ፣ የአስተዳደር ሰራተኞች ፣ተማሪዎችና የበጌምድር ኮሌጅ መምህራን ተወያይተዋል፡፡ የመወያያ ፅሁፉን ያቀረቡት የበጌምድር መምህራን ኮሌጅ ዲን አቶ ያዜ ሐብቴ በሀገራችን የአምስት መቶ አመታት  የማሽቆልቆል ጉዞ ተገትቶ ፈጣንና ፍትሃዊ እድገት እውን የሆነበት ደረጃ ላይ ተደርሷል ብለዋል ፡፡ አቶ ያዜ አያይዘውም በመጀመሪያዎቹ […]