ማስታወቂያ

                                 ቀን 26/08/2010 ዓ.ም

 

ለአዲስ ትምህርት ፈላጊዎች የክረምት ተማሪዎች በሙሉ

ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ በክረምት (summer) ፕሮግራም በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ ዲግሪ መርሃ ግብር ተማሪዎችን በማሰልጠን ላይ ይገኛል፡፡ በ2010 ዓ.ም የትምህርት ዘመንም የማሰልጠን አቅሙን በማሣደግ በመጀመሪያ ዲግሪ አፕላይድ የትምህርት ዘርፍ በሚከተሉት የትምህርት መስኮች አዲስ ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡

የስልጠና መስኮች

ተ/ቁ ፋኩልቲ/ ኮሌጅ/ ተ.ቁ ትምህርት ክፍል (Department) ትምህርቱን ለማጠናቀቅ በክረምት የሚያስፈልገው ጊዜ
1 ተፈጥሮ ቀመር ሳይንስ 1. ሒሳብ 5 አመት
2. ፊዚክስ 5 አመት
3. ባዮሎጂ 5 አመት
4. ኬሚስትሪ 5 አመት
5. ስታቲስቲክስ 5 አመት
2 ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ 6. ኢኮኖሚክስ 5 አመት
7. ማኔጅመንት 5 አመት
8. አካውንቲግና ፋይናንስ 5 አመት
9. ቱሪዝምና ሆቴል ማኔጅመንት 5 አመት
3 ግብርና አካባቢ ሳይንስ 10. ተፈጥሮ ሃብት አያያዝ 5 አመት
11. እፅዋት ሳይንስ 5 አመት
12. እንስሳት ሳይንስ 5 አመት
13. የደን ሳይንስ

 

5 አመት
14. ፎርቲካልቸር 5 አመት
15. አግሪካልቸራል ኢኮኖሚክስ 5 አመት
 4 ቴክኖሎጅ 16. ኤሌክትሪካልና ኮምፒውተር ምህንድስና 7 አመት
17. ሲቪል ምህንድስና 7 አመት
18. ኬሚካል ምህንድስና 7 አመት
19. መካኒካል ምህንድስና 7 አመት
20. ሀይድሮሊክስ እና ውሀ ሀብት ምህንድስና 7 አመት
21. ኮምፒውተር ሳይንስ 6 አመት
22. ኢንፎርሜሽን ቴከኖሎጅ 6 አመት
23. ኤሌክትሮ ሜካኒካል ምህንድስና 7 አመት
5 የማህበራዊና  ሰብአዊ ሳይንስ 24. እንግሊዘኛ  ቋንቋና ስነ-ፁሁፍ 5 አመት
25. ጆኦግራፊና አካባቢ ጥናት 5 አመት
26. በቅድመ ልጅነት ክብካቤ ትምህርት (ecce) 5 አመት
25. ስነ-ዜጋና ስነ-ምግባር 5 አመት
26 አማርኛ ቋንቋና ስነ-ፁሁፍ 5 አመት
27 ልዩ ፍላጎት ትምህርት 5 አመት
28 ሳይኮሎጅ 5 አመት
29 ሶሾሎጅ 5 አመት

 

 

ለአዲስ ገቢ ተማሪዎች

 • የማመልከቻ ጊዜ፡ከግንቦት 21/2010 ዓ.ም እስከ ሠኔ 8/2010 ዓ. ባሉት ተከታታይ የስራ ቀናት
 • የማመልከቻ ቦታ፡- ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ ሬጅስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት ህንፃ ቁጥር 48
 • የመግቢያ ፈተና መስጫ ጊዜ ፡- ሠኔ 27/2010 ዓ.ም

ለነባርና አዲስ ገቢ ተማሪዎች

 

 • ለአዲስ እና ነባር ተማሪዎች ምዝገባ /ክፍያ/ ጊዜ፣ ቱቶሪያል የሚሰጥብት ጊዜና የማጠቃለያ ፈተና መስጫ ጊዜ በውስጥ ማስታዎቂያ ይገለፃል፡፡

 

                                      ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

                                       የተከታታይ ትምህርት ዳይሬክቶሬት        

0581415874 ለበለጠ መረጃ በዚህ ስልክ ቁጥር ይደውሉ

 ቀን 26/08/2010

 

የቅበላ መስፈርቶች  ለክረምት  ተማሪዎች

 1. 1. የመሰናዶ ትምህርትን ላጠናቀቁ
 • ማንኛውም የመሰናዶ ትምህርት ያጠናቀቀ ተማሪ በየአመቱ ትምህርት ሚኒስቴር የሚያወጣዉን የመቁረጫ ነጥብ የሚያሟላ በሚፈልገው የትምህርት መስክ በዲግሪ መርሃ-ግብር ተመዝግቦ መማር ይችላል፡፡
 1. TVET ተምረው ላጠናቀቁ
 • COC ለወጣላቸው የትምህርት መስኮች በደረጃ 4 የሙያ ብቃት ምዘና ወስደዉ ብቁ የሆኑና ዩኒቨርሲቲዉ የሚሰጠዉን ፈተና ተፈትነዉ ማለፍ ይኖርባቸዋል፡፡
 • COC ላልወጣላቸው የትምህርት መስኮች ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን ፈተና መፈተን የሚችሉና ለመግቢያ የሚሆን ዉጤት ማስመዝገብ መቻል አለባቸው፡፡
 • COC ለወጣላቸውም ሆነ ላልወጣላቸው የትምህርት መስኮች አመልከቾች ከሚሰሩበት ተቋም የአንድ አመት  የስራ ልምድ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 1. 12+2 ዲኘሎማና 12+3 አድቫንስ ዲፕሎማ ላጠናቀቁ
 • 2.00 ነጥብ እና ከዚያ በላይ ውጤት ያላቸው፣ ዕውቅና  ካለው ተቋም ዲኘሎማውን ለማግኘታቸው የሚያረጋግጡና ዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን ፈተና መፈተን የሚችሉ ተመዝግበው መማር ይችላሉ፣
 1. ዲግሪ ያለው ወደ ሌላ ዲግሪ ለመመዝገብ ይፈቀድለታል፡፡
 • ዲግሪውን እና ትራንስክርቢቱን ከሌሎች በሬጅስትራር ከሚጠየቁ ማስረጃዎች ጋር በማቅረብ በሚመርጠው የትምህርት ክፍል ገብቶ መማር ይችላል፡፡
 1. 5. በመምህርነት ሙያ ዲኘሎማ ኖሯቸው ዲግሪ ለመማር የሚፈልጉ አመልካቾች

  በተመሳሳይ የትምህርት መስክ በአኘላይድ ዘርፍ መመዝገብ ይችላሉ፡፡

 

 1. በግብርና ሙያ በዲኘሎማ የተመረቁ አመልካቾች መመዝገብ የሚችሉት በግብርና

   መስኮች ብቻ ነው፡፡

 

ማሳሰቢያ፡-

ለምዝገባ ሲመጡ

 • የምዝገባ ማመልከቻ ክፍያ 30 ብር
 • አንድ 3×4 የሆነ ፎቶግራፍ
 • 12ኛ ክፍል ከሆኑ የ8ኛ፣ የ10ኛ፣ የ12ኛ የትምህርት ማስረጃ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ
 • ዲኘሎማ ከሆኑ የ10ኛ/12ኛ፣ የደረጃ 4 coc፣ ዲኘሎማ ማስረጃ ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ይዘው መምጣት ይጠበቅበዎታል፡፡

 

                     ደብረ ታቦር ዩኒቨርሲቲ

የተከታታይ ትምህርት ዳይሬክቶሬት